የሚጠየቁ ጥያቄዎች
ተደጋግሞ የሚነሱ ጥያቄዎች
መልሱን ከታች ማግኘት ካልቻሉ፣ እባክዎን የእውቂያ ቅጹን ይጠቀሙ ወይም በኢሜል ወደ. addislhria@gmail.com
- ሀገራዊ ደረጃን መሰረት ያደረገ የቁራሽ መሬት ልዩ መለያ ኮድ ይሰጣል፤ ተግባራዊነቱንም ያረጋግጣል፣
- የተረጋገጡ የመሬት ይዞታዎችን ይመዘግባል፣ በአግባቡ መመዝገቡንም ያረጋግጣል፤ ይቆጣጠራል፤
- አግባብ ባለው ህግ መሰረት ለተመዘገቡ የመሬት ይዞታ መብት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ይሰጣል፣መሰጠቱን ያረጋግጣል፣ ይቆጣጠራል፤
- በተመዘገቡ የመሬት ይዞታዎች ላይ የይዞታ አገልግሎቶችን ይሰጣል፤ በአግባቡ መሰጠታቸውን ያረጋግጣል፣ ይቆጣጠራል፤
- የመሰረታዊና የህጋዊ ካዳስተር ካርታ ያዘጋጃል፣ ወቅታዊ ያደርጋል፤
- የመሬት ይዞታ ምዝገባ መረጃን በዲጂታል እና በወረቀት ይይዛል፤ ያደራጃል፤ ይተነትናል፤ ወቅታዊ ያደርጋል፤
- የከተማ መሬት እና መሬት ነክ፣ የፊዝካል መሠረተ ልማትና የማህበራዊ ተቋማት የስፓሻልና ስፓሻል ያልሆኑ መረጃዎችንና ጥናቶችን ከሚመለከታቸዉ ተቋማት ይሰበስባል፣ በመረጃ ቋት ያደራጃል፤ይተነትናል፣ያሰራጫል፤
- አግባብ ባለው ህግ መሠረት ከተማዋን ሙሉ በሙሉ የሚሸፍን የአየር ፎቶ ያነሳል፤ ፎቶውን በመጠቀም መሠረታዊ የካዳስተር ካርታ ወቅታዊ ያደርጋል፣
- እንደ አስፈላጊነቱ የአየር ፎቶ፣ የሳተላይት ምስሎችና የራዳር ፎቶዎች የመሳሰሉ የሪሞት ሴንሲንግ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የግንባታዎች፣ የመሬት አጠቃቀምና ሌሎች የከተማ ለውጦችን በመለየት፤ ለሚመለከታቸው አካላት ውሳኔ እንዲሠጡበት ያስተላልፋል፤ እንደአስፈላጊነቱ ጥሬ መረጃዎችን ለተለያዩ አካላት በሚያቀርቡት ጥያቄ መሠረት ይሠጣል፤
- ከሚመለከተው ባለድርሻ አካል ጋር በመሆን የከተማውን መሬትና መሬት ነክ መረጃ ሥርዓት ላይ የስጋት እና የደህንነት ቁጥጥር ያደርጋል፤ የእርምት እርምጃ ይወስዳል፤
- ሁለ-አቀፍ ካዳስተር ቴክኖሎጂ ስርዓትን እና የኔትዎርክ መሰረተ-ልማትን ያሻሽላል፤ ወቅታዊ ያደርጋል፤ ያስተዳድራል፤
- አግባብ ባለው ህግ መሰረት የሕጋዊ ካዳስተር፣የቋሚ ንብረት መረጃ፣አድራሻ መረጃ፣ መሬትና መሬት ነክ መረጃን ለህዝብ ክፍት ያደርጋል፤
- ተግባሩን በሚመለከት የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ይመረምራል፣ ውሳኔም ይሰጣል፤
- በህግ አግባብ የዋስትና ፈንድ እንዲቋቋም ያደረጋል፣ የዋስትና ፈንዱ ማቋቋሚያ እንዲሆን ክፍያ ይሠበስባል፤ ተቋሙ በሰጠው የምዝገባ ማስረጃ ምክንያት በቅን ልቦና ጉዳት ለደረሰበት ሶስተኛ ወገን በፍርድ ቤት ውሳኔ መሠረት ካሳ ይከፍላል፤
- የመሬት መቆጣጠሪያ ነጥቦችን ሀገራዊ ስታንዳርዶችን መሠረት በማድረግ ይተክላል፤ያስተክላል፣ እንዲናበቡ እና እንዲዘምኑ ያደርጋል፤ ያስተዳድራል፤
- መሬት እና መሬት ነክ መረጃ ለመሰብሰብ፣ ለማደራጀትና ለማሠራጨት፤ የቋሚ ንብረት ምዝገባና ትመና፤ የአድራሻ ሥርዓት ለመዘርጋት፣ ለማስተዳደር እና የቤት ቁጥር ለመስጠት የሚያገለግል የህግ ማዕቀፎችንና ስታንዳርዶችን በማዘጋጀት ያስጸድቃል፤ ሲጻድቅ ተግባራዊ ያደርጋል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
- አድራሻ ሥርዓት ይዘረጋል፣ ያዘምናል፤ ያስተዳድራል፤
- የመንገድ መለያ ኮድና የቤት ቁጥር ይሰጣል፣ ወቅታዊ ያደርጋል፤ በአግባቡ ስለመሠጠቱ ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
- የቋሚ ንብረት መረጃ ይመዘግባል፣ ይይዛል፣ ወቅታዊ ያደረጋል፣የንብረት ግምት/ትመና ይሰራል፣
- በተመዘገቡ ይዞታዎች አግባብ ባለዉ ህግ መሰረት የነባር ይዞታ ኪራይና የቤት ግብር ተመን አስልቶ በህግ ስልጣን ለተሰጠው አካል አገልግሎት ይሰጣል፤
- ኤጀንሲው የተሠጠውን ተልኮ ለማሳካት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ሥራዎችን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ በ3ኛ ወገን/Out Source ሊያሰራ ይችላል፡፡
ተቋሙ የሚሰጡ አገልግሎቶች 22 ናቸው፡፡
ጥያቄህን ጠይቅ
መልሱን ከታች ማግኘት ካልቻሉ እባክዎን መልእክት ይላኩልን.